
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት በድስቱ ማዕከላት ለቢሮ እና ሌሎች አገልግሎቶች ለሚውሉ የህንፃ ግንባታ ስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ተካሄዷል።



ርዕሰ መስተዳድሩ በመርሃ ግብሩ በሁሉም የክልሉ ማዕከላት ሊገነቡ ለታሰቡ የተቋማት ህንፃ ግንባታ ቀድሞ የተጀመሩ ስራዎች የደረሱበትን ደረጃ በተለያየ ጊዜ በመገምገም፤ ግንባታውን በሁሉም ማዕከላት በፍጥነት በመጀመር ባጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የሚያስችል ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡



ርዕሰ መስተዳድሩ የቀደምት ታሪካቸውን በመገምገም በግዜ እና በጥራት ሰርተው የሚያጠናቅቁ በክልሉ የሚገኙ 8 ተቋራጮች የመንግስት የግዥ ህግን በመከተል መመረጣቸውንም አስረድተዋል።



ርዕሰ መስተዳድሩ ተቋራጮቹ ፕሮጀክቱን በተያዘለት የግዜ ገደብ እና የጥራት ደረጃ እንዲሁም በሚፈለገው የአገልግሎት እሳቤ ፈጥኖ መጨረስ ይገባቸዋል ሲሉም አሳስበዋል።



አክለው ፕሮጀክቱ ትልቅ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለስኬታማ አፈጻጸሙ አስፈላጊው ክትትል፣ ቁጥጥር እና ድጋፍ ለዚሁ ዓላማ በተዋቀረ ኮሚቴ የሚደረግ መሆኑንም ተናግረዋል።



በመጨረሻም ርዕሰ መስተዳድሩ በተገኙበት በስድስቱም ማዕከላት ለሚገነቡ የተቋማት የህንፃ ግንባታ ስራው ከየተቋሙ አስተባባሪዎች ጋር የውል ስምምነት ተፈርሟል።