ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ሶዶ ማዕከል የሚገነቡ የቢሮዎች ህንጻ ግንባታ የመስክ ምልከታ አደረጉ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ማዕከል የሚገነባ የርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንፃ ግንባታዎች ጅማሮ የመስክ መልከታ አድርገዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመስክ ምልከታው ወቅት በ9 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባው የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እንዲሁም በ 3 ሄክታር ላይ እየተገነባ የሚገኘውን የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንፃ ግንባታ በተያዘው ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ሊሆን ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

የህንፃ ግንባታዎች በጊዜ መጠናቀቅ ለተቀላጠፈ አግልግሎት አሰጣጥ እና ለስራ ውጤታማነት ሚናው የጎላ መሆኑንም አስረድተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ አክለው የክልሉ መንግስት የታለሙት የህንፃ ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ አስፈላጊውን ክትትል እና ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑንም ተናግረዋል።

በመስክ ጉብኝቱ ከርዕሰ መስተዳድሩ በተጨማሪ የክልሉ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

Leave a Reply