
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ማዕከል የሚገነባ የርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንፃ ግንባታዎች ጅማሮ መስክ ምልከታ በማደረግ የአፈፃፀም ደረጃቸውን ገምግመዋል።



ርዕሰ መስተዳድሩ በመስክ በምልከታቸው ወቅት ህንፃ ግንባታ ከተጀመረ አጭር ጊዜ ቢሆንም የግንባታው ሂደት ጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መመልከታቸውን ገልፀዋል።
ግንባታው በተያዘለት ግዜ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ቀንና ማታ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።



የህንፃ ግንባታው በጊዜ መጠናቀቁ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀው በክልሉ በስድስቱም ክላስተር የተጀመሩ ህንፃዎችን በጥራትና በፍጥነት በመስራት ለአገልግሎት ዝግጁ ሊሆን ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።





ርዕሰ መስተዳድሩ የህንፃ ግንባታዎች በተያዘላቸው ጊዜ ውስጥ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ክትትል እና ድጋፍ ማድረጉን የሚቀጥል መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል።