ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቻችን የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገለጹ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቻችንን የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጽዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያስተላለፉት መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡-

በክልላችን በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በጣለው ከፍተኛ ዝናብ ምክንያት  ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የውድ ወገኖቻችንን ህይወት አጥተናል። 

በዚህ እጅግ ልብ ሰባሪ በሆነ ድንገተኛ አደጋ ባጣነዉ የወገኖቻችንን ህይወት የተሰማኝን ጥልቅ ሐዘን እየገለጽኩ፤ ነፍሳቸዉን በአፀደ ገነት ፈጣሪ ያኑሪልን።

ለቀሪ ቤተሰቦች መፅናናትን እመኛለሁ።

በዚህ አጋጣሚ በክልላችን የክረምቱ ዝናብ መጠናከር ጋር ተያይዞ ለአደጋ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ተመሳሳይ አደጋ እንዳይከሰት አስፈላጊዉ ጥንቃቄ እንዲደረግ ለሁሉም መዋቅር መልዕክት በማስተላለፍ የየራሳችን ኃላፊነት እድንወጣ አደራ እላለሁ።

Leave a Reply