
በክልሉ በጎፋ ዞን የልማት ስራዎችን ጉብኝት እየደረጉ የሚገኙት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የክልሉ ጤና ቢሮ በሳውላ ከተማ የተገነባውን የጎፋ ዞን ሳውላ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት መርቀው በይፋ አገልግሎት አስጀምረዋል።


ርዕሰ መስተዳድሩ የደም ባንክ አገልግሎቱ ማስጀመር ብቻ ሳይሆን በአግባቡ አገልግሎት መስጠት እንዲችል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ህዝቡን በማስተባበር ደም በመለገስ የሰው ህይወት እንዲታደግ ጥሪ አቅርበዋል።



ርዕሰ መስተዳድሩ በመርሃ ግብሩ ደም በመለገስ አገልግሎቱን በይፋ አስጀምረዋል።