ርዕሰ መስተደድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ማሻባ ችግኝ ጣቢያ ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝቱ ችግኝ ጣቢያ ለወጣቱ ስራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ትልቅ ፀጋ በመሆኑ በአግባቡ ማልማትና መጠቀም ያስፈልጋል ብለዋል።
ችግኝ ጣቢያ ትልቅ ኢንቨስትመንት እንደሆነ የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ ለወጣቱ ስራ ዕድልን የሚፈጠር፣ ትልቅ አቅምና ፀጋ እንደሆነም አስገንዝበዋል።
ከተሞችን የሚያስውቡ ችግኞችን የማፍላት ሥራ መሰራት እንደሚገባ ያሳሰቡት ርዕሰ መስተዳድሩ ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች ማባዛት እንዳለበትም አሳስበዋል።
አካባቢው ትልቅ የመልማት ፀጋ ያለው በመሆኑ ሁሉንም አማራጮች በመጠቀም ለከተማው የሚበቃ ሀብት ማፍራት ያስፈልጋል ነው ያሉት።
ችግኝ ጣቢያው በልዩ ትኩረት በመስጠት ማልማት እንደሚገባም አሳስበዋል።
ከችግኝ ጣቢያ በተጨማሪ ለህብረተሰቡ የሰርግ፣ የስብሰባ መዝናኛ ማዕከል እንዲሆን መሰራት እንዳለበትም አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ማሻባ ችግኝ ጣቢያው ከአምስት ሄክታር መሬት በላይ ያረፈ ሲሆን የተለያዩ ዝሪያ ያላቸው ችግኞችን በማፍላት የሚታወቅ መሆኑን ተገልጿል።



