ወላይታ ሶዶ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እጅግ ደማቅ አቀባበል በማድረግ ታላቅ አክብሮቷንና ፍቅሯን ገልጻለች!

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ በጉብኝታቸው በክልሉ በወላይታ ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡ 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ጋር ለጉብኝቱ የሰላም፥ የፍቅርና የአንድነት ሰገነቷ ለምለሚቷ ወላይታ ሶዶ ከተማ ሲደርሱ በሀገር ሽማግሌዎች፤ በዞኑና በከተማ አስተዳደሩ አመራሮች እንዲሁም በመላው የከተማዋ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቱሩ እና ቀዳማይት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በወላይታ ዞን በነበራቸው ቆይታ ከወላይታ ሶዶ ከተማ ጀምሮ በየደረሱበት ህዝቡ እጅግ ደማቅ እና ልብ የሚያሞቅ ልዩ አቀባበል በማድረግ ልባዊ ፍቅሩንና አክብሮቱን ገልጿላቸዋል።

Leave a Reply