የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት አመራሮች በጽ/ቤቱ የ2018 ዕቅድ እና በወቅታዊ ሥራዎች ዙሪያ መከሩ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎችና አማካሪዎች በጽ/ቤቱ የ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ዕቅድ መደበኛ ተግባራት እና በወቅታዊ ሥራዎች ዕቅድ ትግበራ ዙሪያ መክረዋል። 

በምክክሩ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ ቦሻ ቦንቤ (ዶ/ር) በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ስራዎችን በዕቅድ በመምራት እና በጠንካራ የድጋፍና ክትትል ስርዓት በመደገፍ በክልሉ የተሻለ አፈጻጸም እንዲመዘገብ ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡     

ኃላፊው አክለው በክልሉ የጽሕፈት ቤቱ ጠንካራ ተቋማዊ አፈጻጸም እና ውጤታማ የድጋፍና ክትትል ስራዎች በየደረጃው ላሉ አስፈጻሚ ተቋማት ውጤታማነት ወሳኝ መሆኑንም ገልጸው፤ በ2018 በጀት ዓመትም ለላቀ ውጤታማነት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡    

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ዱፄ ታምሩ በበኩላቸው፥ በክልሉ ባለፉ ጊዜያት የክልሉን ህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጀ በደረጃ ምላሽ በመስጠት በተከናወኑ ስራዎች አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ጠቅሰው፤ ጽ/ቤቱ በ2018 በጀት ዓመት በየደረጃው ያሉ የክልሉ አስፈጻሚ ተቋማት እና የታችኛው የአስተዳደር መዋቅሮች አፈጻጸምን በማላቅ የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለዚህም የመደበኛ ዕቅድ ተግባራት እና የወቅታዊ ሥራዎች ዕቅድ ትግበራ ውጤታማነትን በማረጋገጥ በክልሉ የተጀመረውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

ምክክሩ በክልሉ የክልል ማዕከላት የአስፈጻሚ ተቋማት ውጤታማ የመደበኛና በንቅናቄ የሚመሩ ወቅታዊ ስራዎችን ጨምሮ በተዋረድ ያሉ የአስተዳደርና የክልል ተቋማት ተግባራትን ችግር ፈቺ በሆነ የተቀናጀ የድጋፍና ክትትል ስርዓት በመምራት የበጀት ዓመቱን የልማት ግቦች ከግብ ማድረስ የሚያስችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተጠናቋል፡፡

Leave a Reply