የክልሉ የፊሲካል ፖሊስ አፈፃፀም በእጅጉ አዳጊና ተስፋ ሰጪ ነዉ -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ ሕዝብ ምክር ቤትና የብሔረሰቦች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የክልሉ ፊሲካል ፖሊስ አፈፃፀም በእጅጉ አዳጊና ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልጸዋል።

የክልሉ መንግስት የውስጥ አቅምን ለማጎልብት ለገቢ አሰባሰብ ስራው ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ የክልሉ የዉስጥ ገቢ የመሰብሰብ አቅም ከ2016 በጀት አመት ጋር ሲነጻጸር በባለፈዉ ዓመት 45 ከመቶ በላይ ብልጫ የተመዘገበበት መሆኑን አንስተዋል።

ይህ ዕድገት በክልሉ ከፍተኛ የሆነ እምቅ የገቢ አቅም መኖሩን አመላካች ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ በ2018 የክልሉን የገቢ መሰረት በማስፋትና የገቢ አሰባሰብ ተግባርን በልዩ ትኩረት በተቀናጀ አግባብ በመምራት ከታቀደው 30 ቢሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ መስራት እና 75 በመቶ ወጪን በውስጥ ገቢ መሸፈን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ለገቢ አሰባሰብ ስራው ውጤታማነት በገቢ አጀንዳ ዙሪያ በየደረጃው መግባባት በመፍጠር የጋራ ኃላፊነት ማድረግ፣ የገቢ ሴክተር ተቋማዊ አቅምን ማጎልበት፥ አዳዲስ የታክስ መሰረቶችን ለማስፋት ከባቢያዊ ጥናትን መሰረት አድርጎ መስራት እና በሂደቱ ለሚያጋጥሙ ችግሮች ጠንካራ የተጠያቂነት ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

Leave a Reply