ከመላው ኢትዮጵያ ለ19ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ የመጡ የብሔ/ብ/ሕ ልዑካን ቡድኖች አርባ ምንጭ ከተማ ሲደርሱ እጅግ ደማቅ የሆነ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ልዕካን ቡድኖቹ በሰላም አርባ ምንጭ ከተማ የደረሱ ሲሆን፤ በአቀባበል መርሃ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
የብሔሮች፤ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የባህል አምባሳደር የሆኑት ሉዕካን ቡድኖቹ፤ በትላንትናው ዕለት በክልሉ ወላይታ ዞን ሲደርሱ፤ ወላይታ ሶዶ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ የዞኑ ከተሞች እጅግ ደማቅና ልዩ የሆነ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን፤ አስቀድሞ በተያዘው መርሃ ግብር መሰረትም ሉዕካን ቡድኖቹ በወላይታ ሶዶ ከተማ የአንድ ቀን ቆይታ በማድረግ አስደሳች የአብሮነት ጊዜ አሳልፈዋል።
19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን “ሀገራዊ መግባባት ለኀብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በክልሉ አዘጋጅነትና በአርባ ምንጭ ከተማ አስተናጋጅነት የክልሉን ገፅታ በሚያጎላ እና ያሉ ፀጋዎችን በሚያስተዋውቅ መንገድ ከህዳር 25 ጀምሮ በበርካታ ደማቅ ኩነቶች ታጅቦ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡