ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ለይፋዊ የስራ ቆይታ በክልሉ ጅንካ ማዕከል ሲደርሱ እጅግ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፤ ለይፋዊ የስራ ቆይታ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ በኦሪ ዞን ጅንካ ከተማ ገብተዋል፡፡

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ ጅንካ ከተማ ሲደርሱ በክልሉ የጅንካ ማዕከል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፤  የአሪ ዞን ፣ የደቡብ ኦሞ ዞን አመራሮች፤ በሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም በከተማው ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በብዝኃነት ተምሳሌቷ ጅንካ ከተማ ሲደርሱ፤ በክልሉ የጅንካ ማዕከል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፤ በኦሪ እና በደቡብ ኦሞ ዞን ከፍተኛ አመራሮች፤ በሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም በከተማዋ ነዋሪዎች እጅግ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡  

ርዕሰ መስተዳድሩ ለይፋዊ የስራ ቆይታው ጅንካ አየር ማረፍያ መድረሳቸውን ተከትሎ በከተማው በተንቀሳቀሱባቸው ስፍራዎች ሁሉ መላው የአካባቢው ህብረተሰብ እና የከተማው ነዋሪ እጅግ ባማረና በደመቀ መልኩ ልባዊ ፍቅሩንና ጥልቅ አክብሮቱን ገልጾላቸዋል፡፡ 

ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ የመደመር መንግስት ምስረታን ተከትሎ ከዚህ ቀደም በወላይታ ዞን፤  በወላይታ ሶዶ ማዕከል፤ በጋሞ ዞን፤ በአርባምንጭ ማዕከል፤ በጌዴኦ ዞን፤ በዲላ ማዕከል እንዲሁም በጎፋ ዞን በሳውላ ማዕከል እጅግ ደማቅ የሆነ ህዝባዊ አቀባበል የተደረገላቸው መሆኑም የሚታወስ ነው፡፡

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በጅንካ ማዕከል ቆይታቸው ከኦሪ እና ደቡብ ኦሞ ዞን ከተውጣጡ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮችና አመራሮች ጋር በሰላም፣ በመልካም አስተዳደርና በልማት ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክሩ ሲሆን፤ ሌሎች መንግስታዊ ስራዎችንም የሚያከናውኑ ይሆናል።

በክልሉ አዲሱ የመደመር መንግስት ርዕሰ መስተዳድሩ ባስቀመጡት አቅጣጫና በሰጡት የስራ መመሪያ መሰረት፤ በጊዜ የለንም መንፈስ ፈጥኖ ወደ ስራ በመግባት ለክልሉ ህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ምላሽ ከመስጠት ባሻገር ክልሉን የሰላም፤ የፍትህና የብልጽግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ሰንቆ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

Leave a Reply