ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በክልሉ ያደረጉትን የሁለት ቀን የስራ ቆይታ እጅግ አስደሳችና ስኬታማ በሆነ አግባብ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሁለት ተከታታይ ቀናት ያደረጉትን የስራ ቆይታ እጅግ አስደሳችና ስኬታማ በሆነ አግባብ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት በዚሁ የምስጋና መልዕክት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለክልሉ ላደረጉት ሁለተናዊ ድጋፍ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

የርዕሰ መስተዳድሩ የምስጋና መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፦

አክብሮ በመከበር የሚታወቀው

አልምቶ በመልማት የምጠቀሰዉ።

የተፈጥሮ ፀጋ ባለቤት

የታታሪነት ተምሳሌት

የፍቅር እና የሠላም ሰገነት።

ደቡብ ኢትዮጵያ

ከትናንት ነሃሴ 09/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በክልላችን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ እና ሌሎች ሚኒስትሮች ያደረጉት የሥራ ጉብኝት ለመላዉ ክልላችን አመራሮች መነቃቃትን የፈጠረ፣ ተጨማሪ ጉልበት ጥበብና አቅም ያገኘንበት የተሳካ ጊዜ ነበረን። 

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ለሁለተናዊ ድጋፍዎ ከልብ አመሰግኖታለሁ።

መላዉ ህዝባችን እንደተለመደዉ መሪያችንን በክብር ተቀብላችሁ ላከበራችሁ እና ለተከበራችሁ አክብሮትና አድናቆቴ ይድረሳችሁ።  ቀጣይም ጠንክረን በመስራት የክልላችን ራዕይ በህዝባችን ባለቤትነት እናሳካለን። 

ፈጣሪ አብዝቶ ይባርከን!

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

Leave a Reply