Eden Nigussie

Eden Nigussie

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ በክልሉ መንግሥት የ2017 በጀት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

መስተዳድር ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት በአርባምንጭ ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ስብሰባው የክልሉ መንግስት የ2017 በጀት አመት የበጀት ዕቅድ ላይ በዝርዝር ተወያይቷል፡፡ መስተዳድር ምክር ቤቱ ባካሄደው በዚሁ ስብሰባው የክልሉን መንግስት የ2017 ዓ/ም በጀት 37,600,566,984 (ሰላሳ ሰባት ቢሊዮን ስድስት መቶ ሚሊየን አምስት መቶ…

የክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት የክልሉን የ 2017 በጀት ማከፋፈያ ረቂቅ ቀመር መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ

 የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት 1ኛ ዙር 1ኛ ጉባኤዉን በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ አካሂዷል። ምክር ቤቱ ባካሄደው 1ኛ ዓመት 1ኛ ዙር 1ኛ ጉባኤው የክልሉን በጀት ማከፋፈያ ቀመርን ጨምሮ የምክር ቤቱን የአሠራርና የአባላት የስነ ምግባር ደንብ፣ የ 2016…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ሶዶ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራን ጎበኙ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ዞን የልማት ስራዎችን በመጎብኘት ላይ ሲሆኑ በጉብኝታቸው በወላይታ ሶዶ ከተማ በመከናወን ላይ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት ስራ ጎበኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ በከተማው በመከናወን ላይ የሚገኘውን የኮርደር ልማት ስራ አድንቀው በክልሉ የከተማውን ኀብረተሰብ የልማቱ ባለቤት በማድረግ…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ሶዶ ከተማ የልማት ስራዎችን ጎበኙ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ  በወላይታ ሶዶ ከተማ ባደረጉት የልማት ስራዎች ጉብኝት የኢትዮ-ቺክን የለማ እንቁላል ማምረቻ ማዕከልን ጎበኝተዋል፡፡ የጉብኝቱ ዋና ዓላማ በክልሉ በግል ባለሀብቱ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን በመመልከት ተቀናጅቶ መስራት የሚቻልበትን አግባብ ለማመቻቸት መሆኑም ተገልጿል፡፡ ኢትዮ-ቺክን የግል ኩባንያ በዓመት ከ70…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

መስተዳድር ምክር ቤቱ 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን በወላይታ ሶዶ ከተማ ያካሄደ ሲሆን፤ በስብሰባው የክልሉን መንግስት የ2016 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም እና በ2017 ዕቅድ ዝግጅት ዙሪያ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። መስተዳድር ምክር ቤቱ በስብሰባው በዋናነት የበጀት አመቱን የክልሉ መንግሰት አጠቃላይ የስራ…

“ግብርን በወቅቱ በታማኝነት መክፈል ሀገርን የማልማት እና የመገንባት የሚያኮራ የዜግነት ተግባር ነው!”  ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ዓመታዊ የግብር መክፈያ ወቅትን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ግብር የተጫነብን ግደታ ሳይሆን እንደ ዜጋ ማህበራዊ ኃላፊነታችንን በመወጣት የምንፈጽመው የሚያኮራ የዜግነት ተግባር መሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል፡፡ ግብርን በወቅቱ በታማኝነት መክፈላችን እንደ ዜጋ ለሀገራችን ልማት የድርሻችንን…

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ከሐምሌ 1 ጀምሮ ለሚጀመረው የዘመኑ የገቢ ግብር አሰባሰብ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ሁሉም ዞኖች ከሐምሌ 1 ጀምሮ ለሚጀመረው የዘመኑ የገቢ ግብር አሰባሰብ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል። በክልሉ ዘንድሮ ለገቢ አሰባሰብ ስርዓቱ በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ከመቸውም ጊዜ በላይ የገቢ አሰባሰብ ስራዉ በተደራጀ እና በተቀናጀ አግባብ…

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ( ዶ/ር)  በጋሞ ዞን ቁጫ ወረዳ በሰላምበር ከተማ የስራ ጉብኝት አድርገዋል

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ( ዶ/ር)  በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን እያደረጉ ባሉት የስራ ጉብኝት ወደ ቁጫ ወረዳ በመጓዝ በሰላምበር ከተማ የስራ ቆይታ አድርገዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚሁ የስራ ጉብኝት ሰላምበር ሲደርሱ በመላው የወረዳው ህዝብ እጅግ ደማቅ የሆነ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምረቃ ወቅት መልዕክት አስተላልፈዋል

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን በመሰረትን የመጀመሪያ ዓመት የማህበራዊ ብልፅግናችን ትልም ማሳኪያ የሆነው ሰው ተኮር ፕሮጀክታችንን ማስመረቅ በመቻሉ ፈጣሪን አመሰግናለሁ ብለዋል። ክልላችን የተፈጥሮ ፀጋዎች መናገሻ፤ የብሔር ብሔረሰቦች መድመቅያ፤ የሰላምና የመቻቻል ተምሳሌት፤ የአብሮነትና የፍቅር ሙዳይ፤ የጥበብ መፍለቅያ፤ የትጉ እና የታታሪ…

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በይፋ ተመረቀ

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በይፋ ተመርቋል። ግንባታው በመጋቢት 2007 ዓ.ም የተጀመረው ሆስፒታሉ በ25 ሺህ ካሬ ላይ ያረፈ ግዙፍና እጅግ ዘመናዊ ሆስፒታል ነው፡፡ ሆስፒታሉ የሄሊኮፕተር አምቡላንስ አገልግሎት ጭምር እንዲሰጥ ታስቦ…