በኅብረት ዳግም ታሪክ መስራት ችለናል!

ዛሬ ሐምሌ 24/2017 ዓ/ም በሀገራዊው የአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ተከላ በክልላችን ዘርፌ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን 60 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል አቅደን፤ በክልሉ ህዝብ ግንባር ቀደም ተሳትፎ ከዕቅድ በላይ 69 ሚሊዮን ችግኞች በመትከል ለአገራዊ ግብ ስኬት የድርሻችንን በማበርከት ሌላ ታሪክ ማስመዝገብ በመቻላችን የተሰማኝን ልባዊ ደስታ እየገለጽኩ ለመላው የክልሉ ህዝብ የላቀ ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡   

የተመዘገበው ስኬት እጅ ለእጅ ተያይዘን በአንድ መንፈስ ያቀድነውን ለማሳካት ከተረባረብን የማናሳካው ግብ አለመኖሩን የዕለቱ የአንድ ጀንበር ተከላ አስደናቂ ስኬታችን ተጨባጭ ማሳያ በመሆኑ፤ በቀጣይም በሁሉም የልማት መስኮች በጀመርናቸው ስራዎች በህዝባችን ግንባር ቀደም ተሳትፎ በአንድ መንፈስ በጋራ በመረባረብ የክልላችንን የሰላም፤ የልማትና የሁለንተናዊ ብልፅግና ረዕይ የሚናረጋግጥ ይሆናል፡፡   

በዕለቱ በመላዉ የክልላችን ህዝቦች ፅናት እና ትጋት ለተመዘገበው ስኬት በማስተባበርና በመምራት ጉልህ አስትዋጽኦ ላበረከታችሁ እንዲሁም ከማለዳ እስከ ምሽት በትጋት ለተከላችሁ በሙሉ ዳግም ልባዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩ፤ በቀጣይ የተተከሉትን በመንከባከብና በመጠበቅ ደህንነቱ የተጠበቀ አረንጓዴ ከባቢን ለትውልድ ለማሻገር እንድንተጋ አሳስባለሁ፡፡   

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!!

Leave a Reply