
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!” በሚል መሪ ቃል በዲመካ ከተማ ከሁሉም መዋቅሮች የተወጣጡ ብሄር ብሄረሰቦች በተገኙበት ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ ተካሂዷል።



በመርሃ ግብሩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ርዕሰ መስተዳድሩ፡- ደቡብ ኦሞ ዞን የብዝሃ ፀጋ ባለቤት፣ የታታሪዎች መናሃሪያ፣ የትሁቶች መንደር፣ የሰላም ሰገነት ለኢትዮጵያ መሰረት ሆኖ ድንብር የሚጠብቅ በፍቅር በአንድነት የሚታወቅ ታላቅ ህዝብ ነው ሲሉ ተናግረዋል።



ደቡብ ኦሞ ዞን የብልፅግና ቱሩፋት መሆኑን የጠቀሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ባለፉት ሶስት ዓመታት የዞን ማዕከል በመሆን የተለያዩ የልማት ስራዎች በመስራት ለውጥ በማስመዝገብ ላይ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዋል።
ፓርቲው በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ዜጋ ተኮር ስራዎች ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በመስራት የዜጎችን ቁልፍ ጥያቄ ከመመለስ ባለፈ፤ ለመጪው ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማሻገር አቅዶ የሚሰራና ሁሉንም በእኩል የሚያይ ፓርቲ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡



ብልፅግና በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን በመለየት በራስ አቅም ኢትዮጵያን የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት የማድረግ ራዕይ ሰንቆ እየተጋ የሚገኝ፤ በተጨባጭ ውጤትም የወደፊት ብሩህ ተስፋን አሻግሮ ማየት ያስቻለ ፓርቲ መሆኑን ጨምረው ተናግረዋል።



ርዕሰ መስተዳድሩ ደቡብ ኦሞ ዞን የአንድነትና የወንድማማችነት ተምሳሌትነትን እና የብዝኃነት ጥንካረን በተግባር ያሳየ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዞኑ 15 ብሄረሰቦች ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በኅብረትና በአንድነት ከዞኑ አልፈው ሀገር በማልማቱ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከቱ እንደሚገኝ ገልፀዋል።



ፓርቲው የምርጡኝ ቅስቀሳ ሲያደርግ ባለፉት 8 ዓመታት በተሰሩ ስራዎች የተመዘገቡ አመርቂ ውጤቶችን በማስፋት እንዲሁም አዳዲስ ፕሮግራሞችን እውን በማድረግ ኢትዮጵያን ከፍ የሚያደርግ ስራ ሰርቶ ነገ የተሻለች ኢትዮጵያ ለትውልድ ለማሻገር የሚያስችል በርካታ ፕሮግራሞችን ቀርጾ መሆኑንም ተናግረዋል።
ብልፅግና ዛሬን ተዘጋጅቶ፣ ነገን አልሞ፣ የወደፊቱን አስቦ የሚሰራ ፓርቲ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ይህን ፓርቲ መምረጥ ሀገርን ወደ ብልፅግና ማማ ማሻገር መሆኑን በአጽንኦት ገልፀዋል፡፡



ርዕሰ መስተዳድሩ በመጨረሻም ተጋግዘንና ተደጋግፈን የጀመርነውን የብልፅግና ጉዞ ለማስቀጠል፤ የአንድነት የኅብረት እና የመደጋገፍ ምሳሌ የሆነውን የስንዴ ነዶን ምረጡ፤ መጪው ጊዜ ከብልፅግና ጋር ብሩህ ነው በማለት መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።

የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገብረ መስቀል ጫላ በበኩላቸው፤ ብልፅግና ፓርቲ ቃልን በተግባር ያሳየ፤ የዜጎችን መብት የሚያከብርና የህዝቦች እኩልነት ያረጋገጠ፤ ዳር የነበረውን ወደ መሃል ያመጣ ፓርቲ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
ብልፅግና ድህነትን ታሪክ ለማድረግ ባለው ቁርጠኝነት የታሪክ ዕጥፋት በማስመዝገብ ጭምር ስንዴን ወደ ውጪ በመላክ የተረጂነትን ታሪክ የቀየረ ፓርቲ ነው ያሉት ኃላፊው፤ የተጀመረውን ልማት ለማስቀጠል ብልፅግናን እንዲመርጡ ጥሪ አቅርበዋል።




