Category Press Statements

Press Statements

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን በደረሰው ድንገተኛ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን አጽናኑ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኮርያ የነበራቸውን የስራ ቆይታ አቋርጠው በመመለስ በጎፋ ዞን በደረሰው ድንገተኛ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖቻችንን አጽናንተዋል፡፡ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን፤ ገዜ ጎፋ ወረዳ፤ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ ሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም የተከሰተ ድንገተኛ የመሬት…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰ የመሬት ናዳ ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ቀበሌ በዛሬው ዕለት በአከባቢው ከጣለው ከፍተኛ ዝናብ ጋር ተያይዞ በደረሰ የመሬት ናዳ በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ዛሬ ረፋድ አራት ሠዓት ገደማ በጎፋ ዞን ገዜ…

አቶ ገብረመስቀል ጫላ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሆነዉ ተሾሙ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ያቀረቡትን ሹመቶች ተቀብሎ አፅድቋል፡፡ በዚህ መሰረት አቶ ገብረመስቀል ጫላ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፤ የአርባ ምንጭ ክላስተር…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የክልሉን መንግስት የ2017 በጀት 37.6 ቢሊየን ብር አፀደቀ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት እያካሄደ ባለው 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ጉባኤ በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ተወስኖ የቀረበለትን የክልሉን መንግስት የ2017 ረቂቅ በጀት አስመልክቶ በጥልቀት ተወያይቷል፡፡ ምክር ቤቱ በመስተዳድር ምክር ቤት የቀረበውን የክልሉን መንግስት የ2017 ረቂቅ…

የደቡብ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ለዞን አስተዳደር እርከኖች ለ2017 በጀት አመት 30 ቢሊየን ብር በጀት እንዲመደብ ውሳኔ አሳለፈ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የ2017 በጀት በተመለከተ ከዞን አስተዳደር እርከን አመራሮች ጋር በአርባምንጭ ከተማ ተወያይተዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ የህዝቡን የልማት ጥያቄዎችና የመልማት ፍላጎቶች ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ በማሰብ በ2017 በጀት ዓመት የበጀት ድልድል የክልሉን ድርሻ በእጅጉ በመቀነስ የዞኖችን ድርሻ ከፍ ለማድረግ በመስተዳድር…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ በክልሉ መንግሥት የ2017 በጀት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

መስተዳድር ምክር ቤቱ በዛሬው ዕለት በአርባምንጭ ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ስብሰባው የክልሉ መንግስት የ2017 በጀት አመት የበጀት ዕቅድ ላይ በዝርዝር ተወያይቷል፡፡ መስተዳድር ምክር ቤቱ ባካሄደው በዚሁ ስብሰባው የክልሉን መንግስት የ2017 ዓ/ም በጀት 37,600,566,984 (ሰላሳ ሰባት ቢሊዮን ስድስት መቶ ሚሊየን አምስት መቶ…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

መስተዳድር ምክር ቤቱ 13ኛ መደበኛ ስብሰባውን በወላይታ ሶዶ ከተማ ያካሄደ ሲሆን፤ በስብሰባው የክልሉን መንግስት የ2016 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም እና በ2017 ዕቅድ ዝግጅት ዙሪያ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። መስተዳድር ምክር ቤቱ በስብሰባው በዋናነት የበጀት አመቱን የክልሉ መንግሰት አጠቃላይ የስራ…

“ግብርን በወቅቱ በታማኝነት መክፈል ሀገርን የማልማት እና የመገንባት የሚያኮራ የዜግነት ተግባር ነው!”  ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ዓመታዊ የግብር መክፈያ ወቅትን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ግብር የተጫነብን ግደታ ሳይሆን እንደ ዜጋ ማህበራዊ ኃላፊነታችንን በመወጣት የምንፈጽመው የሚያኮራ የዜግነት ተግባር መሆኑን መገንዘብ ይገባል ብለዋል፡፡ ግብርን በወቅቱ በታማኝነት መክፈላችን እንደ ዜጋ ለሀገራችን ልማት የድርሻችንን…

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ከሐምሌ 1 ጀምሮ ለሚጀመረው የዘመኑ የገቢ ግብር አሰባሰብ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ሁሉም ዞኖች ከሐምሌ 1 ጀምሮ ለሚጀመረው የዘመኑ የገቢ ግብር አሰባሰብ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታውቋል። በክልሉ ዘንድሮ ለገቢ አሰባሰብ ስርዓቱ በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ከመቸውም ጊዜ በላይ የገቢ አሰባሰብ ስራዉ በተደራጀ እና በተቀናጀ አግባብ…

“ገበታ ለትውልድ በምድረ ገነቷ አርባምንጭ ለመላው ኢትዮጵያውን ዕድል ይዞ ቀርቧል” ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ በከተማው በማድረግ ላይ ያሉትን የስራ ጉብኘት አስታከው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በመልዕክታቸውም አርባ ምንጭ የፍራፍሬ ቅርጫት ከመሆኗም በላይ…