News

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአርባ ምንጭ ከተማ የኮሪደር ልማት ስራ፤ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት እና ሌሎች የግብርና የልማት ስራዎችን ጎበኙ      

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሕዳር 29 ቀን 2017 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ ለሚከበረው 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል አርባምንጭ ከተማ ገብተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለክብረ በዓሉ አርባምንጭ አለም አቀፍ አይሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ደማቅ…

ለ19ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመጡ የብሔ/ብ/ሕ ልዑካን ቡድኖች አርባ ምንጭ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

ከመላው ኢትዮጵያ ለ19ኛው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ የመጡ የብሔ/ብ/ሕ ልዑካን ቡድኖች አርባ ምንጭ ከተማ ሲደርሱ እጅግ ደማቅ የሆነ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።   ልዕካን ቡድኖቹ በሰላም አርባ ምንጭ ከተማ የደረሱ ሲሆን፤ በአቀባበል መርሃ ግብሩ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣…

ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ የወላይታ ሶዶ የኢቢሲ ተጨማሪ የይዘት ምንጭ ስቱዲዮን በይፋ መርቀው ከፈቱ

ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ እና የፌደራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የወላይታ ሶዶ የኢቢሲ ተጨማሪ የይዘት ምንጭ ስቱዲዮን በይፋ መርቀው ከፍተዋል።    ርዕሰ መስተዳድሩ በምረቃው ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት ገለልተኛ፤ ኢትዮጵያን የሚመስል የሚዲያ ተቋም ለመገንባት ባደረገው ሪፎርም መሰረት፤ የኢቢሲ የይዘት አድማስን…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የክልሉን የገጠር መንደሮች በአማራጭ ኢነርጂ የመብራት ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ከኢትዮ-ቻይና የወዳጅነት ትብብር ኮሚቴ ጋር ተፈራረሙ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በክልሉ ማዕድንና ኢነርጅ ዘርፍ፤ በተለይም የገጠሩን ህብረተሰብ በአማራጭ የኢነርጂ ኃይል የመብራት ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ የልማት ትብብር ዙሪያ ከኢትዮ-ቻይና የወዳጅነት ትብብር ኮሚቴ አባላት ጋር  በአርባ ምንጭ ከተማ በመወያየት የድጋፍ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡  ርዕሰ መስተዳድሩ በውይይቱ ኢትዮጵያ እና ቻይና…

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት ባካሄደው 18ኛ መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ      

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት፤ ዛሬ በበይነ መረብ ባካሄደው 18ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዪ አጀንዳዎቸ ላይ ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል። መስተዳድር ምክር ቤቱ በ18ኛ መደበኛ ስብሰባው በመንግስት ሰራተኞች የደምወዝ ማሻሻያ መመሪያ፣ የልማት ተነሺዎች ምትክ መሬት ማስተላለፍ፣ 19ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና…

የደቡብ ኢትዮጰያ ክልል 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓልን በተሻለ መልኩ በድምቀት ለማክበር የሚያስችል ዝግጅት በማድረግ ላይ ይገኛል -ክቡር አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል “ሀገራዊ መግባባት ለኀብረ-ብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት፤ በአርባ ምንጭ ከተማ ከህዳር 25 እስከ ህዳር 29/2017 ዓ.ም በድምቀት ይከበራል፡፡ የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር በዛሬው ዕለት…

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ሕብረብሔራዊ አንድነት እንዲጠናከር እና ዴሞክራሲያዊ ልምምድ እንዲዳብር የሚያደርግ ነው – ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ  

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ 19ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል አከባበርን በማስመልከት በዛሬው ዕለት በአርባ ምንጭ ከተማ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።    ርዕሰ መስተዳድሩ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዘጋጅነት ሀገራዊ መግባባት ለኅብረብሔራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል ህዳር 29/2017 ዓ/ም የሚከበረው 19ኛው የኢትዮጵያ…

“ክልሉ በቡና እና ቅመማ ቅመም ዘርፍ ያለውን ፀጋ አሟጦ በመጠቀምና የምርት ጥራትና ምርታማነትን በማሳደግ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በመስራት ላይ ይገኛል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ በጌዴኦ ዞን በዲላ ዙሪያ፣ ይርጋጨፌ እና ወናጎ ወረዳዎች ተዘዋውረው የቡና ምርት አሰባሰብና ዝግጅት ያለበትን ደረጃ የመስክ ምልከታ አድርገዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በጉብኝቱ በክልሉ ከሚገኙ የግብርና ፀጋዎች መካከል ቡና እና ቅመማ ቅመም አንዱ መሆኑን ገልፀው፤…