
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በ7ኛ ዙር 1ኛ መስራች ጉባኤው፤ የተከበሩ ተስፋዬ በልጅጌን (ዶ/ር)፤ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በማድረግ ሰይሟል።


በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ዶ/ር ተስፋዬ፤ ሰፊ የፖለቲካ አመራር እና የካበተ የሕዝብና የመንግስት አስተዳደር ልምድ እንዲሁም ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ሲሆን፤ ምክር ቤቱ በሙሉ ድምፅ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በማድረግ ሰይሟቸዋል፡፡
ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በምክር ቤቱ ቃለ መሃላ በመፈፀም ስራቸውን በይፋ የጀምሩ ሲሆን፤ ክልሉን ላለፉት ሦሥት ዓመታት በከፍተኛ ትጋት በርዕሰ መስተዳድርነት ያገለገሉት የተከቡሩ አቶ ጥላሁን ከበደ በጉባኤው ተገኝተው የስራ ርክክብ አድርገዋል፡፡

መልካም የስራ ዘመን!!!




