Category Latest news

የክልሉ ሕዝብ ምክር ቤትና የብሔረሰቦች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የሥራ ዘምን የጋራ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በተገኙበት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ ምክር ቤት እና የብሔረሰቦች ምክር ቤት 6ኛው ዙር 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት በአርባ ምንጭ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በሥነ-ሥርዓቱ ለሁለቱ ምክር ቤቶች ዓመታዊ ሥራቸውን እንደጀመሩ…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለደመራ እና መስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለደመራ እና መስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉየመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለደመራ እና መስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!መስቀል መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰው ልጆች ድኅነት መስዋዕትነት የከፈለበት መንበር በክርስትና እምነት…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጌዴኦ ዞን የደረሰውን አደጋ ተከትሎ የክልሉን የአደጋ ስጋት ምክር ቤት በመሰብሰብ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል 

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጌዴኦ ዞን ባደረጉት የስራ ቆይታ በዞኑ በራጴ ወረዳ የተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ ያደረሰውን ጉዳት በመመልከት በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን በስፍራው ተገኝተው ያፅናኑ ሲሆን፤ የክልሉን የአደጋ ስጋት ምክር ቤት በመሰብሰብም በቀጣይ ተግባራት ዙሪያ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን በስፍራው ተገኝተው አፅናኑ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በክልሉ በጌዴኦ ዞን፤ ራጴ ወረዳ በጫራቃ እና በሀሮ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን በስፍራው በመገኘት አፅናንተዋል።  በአካባቢው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የጣለውን ከፍተኛ ዝናብ ተከትሎ የተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ፤ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ የተገነባ የደም ባንክ መርቀው በይፋ አገልግሎት አስጀምረዋል

በክልሉ በጎፋ ዞን የልማት ስራዎችን ጉብኝት እየደረጉ የሚገኙት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የክልሉ ጤና ቢሮ በሳውላ ከተማ የተገነባውን የጎፋ ዞን ሳውላ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት መርቀው በይፋ አገልግሎት አስጀምረዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ የደም ባንክ አገልግሎቱ ማስጀመር ብቻ ሳይሆን በአግባቡ አገልግሎት…

“እኛ ኢትዮጵያዊያን ከተባበርንና ከተደጋገፍን የማንሻገረው ችግር አለመኖሩን በጎፋ ዞን ተከስቶ የነበረው የተፈጥሮ አደጋን ተከትሎ የተደረገው የተቀናጀ ርብርብና የተገኘው ውጤት ማሳያ ነው”  ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ያስገነባቸውን 296 መኖሪያ ቤቶች በዛሬው ዕለት ለተጎጂዎች አስረክበዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በርክክብ መረሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ማህበሩ አደጋው…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቻችን የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገለጹ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቻችንን የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጽዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያስተላለፉት መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- በክልላችን በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በጣለው…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን በሳውላ ማዕከል ይፋዊ የስራ ቆይታ አደረጉ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለይፋዊ የስራ ጉዳይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወደ ጎፋ ዞን በማቅናት በሳውላ ማዕከል የስራ ቆይታ አድርገዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ ለይፋዊ የስራው ጉዳይ ሳውላ ከተማ ስድርሱ በክልሉ የሳውላ ማዕከል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፤ በጎፋ ዞንና በሳውላ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም…

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት አመራሮች በጽ/ቤቱ የ2018 ዕቅድ እና በወቅታዊ ሥራዎች ዙሪያ መከሩ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎችና አማካሪዎች በጽ/ቤቱ የ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ዕቅድ መደበኛ ተግባራት እና በወቅታዊ ሥራዎች ዕቅድ ትግበራ ዙሪያ መክረዋል።  በምክክሩ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ ቦሻ ቦንቤ (ዶ/ር) በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ስራዎችን በዕቅድ በመምራት…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ሶዶ ማዕከል የሚገነቡ የቢሮዎች ህንጻ ግንባታ የመስክ ምልከታ አደረጉ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ማዕከል የሚገነባ የርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንፃ ግንባታዎች ጅማሮ የመስክ መልከታ አድርገዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በመስክ ምልከታው ወቅት በ9 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባው የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እንዲሁም…