Latest news

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቻችን የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገለጹ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቻችንን የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጽዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያስተላለፉት መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- በክልላችን በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በጣለው…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን በሳውላ ማዕከል ይፋዊ የስራ ቆይታ አደረጉ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለይፋዊ የስራ ጉዳይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወደ ጎፋ ዞን በማቅናት በሳውላ ማዕከል የስራ ቆይታ አድርገዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ ለይፋዊ የስራው ጉዳይ ሳውላ ከተማ ስድርሱ በክልሉ የሳውላ ማዕከል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፤ በጎፋ ዞንና በሳውላ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም…

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት አመራሮች በጽ/ቤቱ የ2018 ዕቅድ እና በወቅታዊ ሥራዎች ዙሪያ መከሩ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎችና አማካሪዎች በጽ/ቤቱ የ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ዕቅድ መደበኛ ተግባራት እና በወቅታዊ ሥራዎች ዕቅድ ትግበራ ዙሪያ መክረዋል።  በምክክሩ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ ቦሻ ቦንቤ (ዶ/ር) በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ስራዎችን በዕቅድ በመምራት…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ሶዶ ማዕከል የሚገነቡ የቢሮዎች ህንጻ ግንባታ የመስክ ምልከታ አደረጉ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ማዕከል የሚገነባ የርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንፃ ግንባታዎች ጅማሮ የመስክ መልከታ አድርገዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በመስክ ምልከታው ወቅት በ9 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባው የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እንዲሁም…

በቴክኖሎጂና በሀገራዊ ኢኒሼቲቮች የታገዘ ግብርናን በማከናወን ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚሰራው ሥራ ይጠናከራል -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በቴክኖሎጂ የታገዘና በሀገራዊ ኢኒሼቲቮች የተቃኘ የግብርና ልማት ሥራ በማከናወን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፥ ክልሉን የሰላም፣የመቻቻልና የብልጽግና ተምሳሌት ማድረግ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የአንጋፋው አርቲስት ፊሻሌ ሚልካኖ እና የሁለት የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ በማስጀመር ክልላዊ የአንድ ጀንበር ቤት ግንባታ ስራን በይፋ አስጀመሩ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ “በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ሃሳብ በመከናወን ላይ የሚገኘው የዘንድሮ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የአንድ ጀንበር ቤት ግንባታ የጥበብ ባለውለታ ለሆነው አርቲስት ፊሻሌ ጨምሮ ለሁለት አቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ በማስጀመር በወላይታ ሶዶ ከተማ መርሃ ግብሩን…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 2ኛ ዓመት ምሥረታን በማስመልከት መልዕክት አስተላለፉ

ርዕሰ መስተዳድሩ በመልዕክታቸው ለመላው የክልሉ ሕዝቦች እንኳን ለታሪካዊው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሁለተኛ ዓመት ምሥረታ አደረሳችሁ፤ አደረሰን ያሉ ሲሆን፤ የመልዕክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- ነሐሴ 13 ክልላችን የፌደሬሽኑ 12ኛው ክልል ሆኖ የተመሠረተበት ታርካዊ ዕለት! እንኳን ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሁለተኛ የምሥረታ ዓመት…

ከውቧ አርባ ምንጭ እስከ ዳሞቷ ፀዳል ወላይታ ሶዶ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ የተቸረ ልባዊ ፍቅርና አክብሮት!!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ባለፉት ሁለት ቀናት ቀዳሚ የብዝኃ ሕዝቦች የጋራ ቤት በሆነው የሰላም፤ የመቻቻልና የብዝኃነት ተምሳሌቱ ክልላችን ያደረጉት የማይረሳ የስራ ቆይታ ለቀጣይ ስኬታማ ጉዟችን አንድምታው ብዙ ነው፡፡   ከዚህም በላይ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ቀዳማይት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በክልላችን…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በክልሉ ያደረጉትን የሁለት ቀን የስራ ቆይታ እጅግ አስደሳችና ስኬታማ በሆነ አግባብ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ የምስጋና መልዕክት አስተላለፉ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለሁለት ተከታታይ ቀናት ያደረጉትን የስራ ቆይታ እጅግ አስደሳችና ስኬታማ በሆነ አግባብ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት በዚሁ የምስጋና መልዕክት ክቡር ጠቅላይ…

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን የነበራቸውን ቆይታ ተከትሎ መልዕክት አስተላልፈዋል

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ በጉብኝታቸው በክልሉ በወላይታ ዞን የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ የወላይታ ዞን ቆይታቸው የወላይታ ሶዶ ከተማን የኮሪደር ልማት፤ በዞኑ በአረካ ከተማ አቅራቢያ በግንባታ…