News

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጌዴኦ ዞን የደረሰውን አደጋ ተከትሎ የክልሉን የአደጋ ስጋት ምክር ቤት በመሰብሰብ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል 

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጌዴኦ ዞን ባደረጉት የስራ ቆይታ በዞኑ በራጴ ወረዳ የተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ ያደረሰውን ጉዳት በመመልከት በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን በስፍራው ተገኝተው ያፅናኑ ሲሆን፤ የክልሉን የአደጋ ስጋት ምክር ቤት በመሰብሰብም በቀጣይ ተግባራት ዙሪያ በመምከር ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል፡፡…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን በስፍራው ተገኝተው አፅናኑ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በክልሉ በጌዴኦ ዞን፤ ራጴ ወረዳ በጫራቃ እና በሀሮ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን በስፍራው በመገኘት አፅናንተዋል።  በአካባቢው ለሁለት ተከታታይ ቀናት የጣለውን ከፍተኛ ዝናብ ተከትሎ የተከሰተው የመሬት ናዳ አደጋ፤ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ የተገነባ የደም ባንክ መርቀው በይፋ አገልግሎት አስጀምረዋል

በክልሉ በጎፋ ዞን የልማት ስራዎችን ጉብኝት እየደረጉ የሚገኙት ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የክልሉ ጤና ቢሮ በሳውላ ከተማ የተገነባውን የጎፋ ዞን ሳውላ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት መርቀው በይፋ አገልግሎት አስጀምረዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ የደም ባንክ አገልግሎቱ ማስጀመር ብቻ ሳይሆን በአግባቡ አገልግሎት…

“እኛ ኢትዮጵያዊያን ከተባበርንና ከተደጋገፍን የማንሻገረው ችግር አለመኖሩን በጎፋ ዞን ተከስቶ የነበረው የተፈጥሮ አደጋን ተከትሎ የተደረገው የተቀናጀ ርብርብና የተገኘው ውጤት ማሳያ ነው”  ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ያስገነባቸውን 296 መኖሪያ ቤቶች በዛሬው ዕለት ለተጎጂዎች አስረክበዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በርክክብ መረሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ማህበሩ አደጋው…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቻችን የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገለጹ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቻችንን የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጽዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ያስተላለፉት መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- በክልላችን በጌዴኦ ዞን ራጴ ወረዳ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በጣለው…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በጎፋ ዞን በሳውላ ማዕከል ይፋዊ የስራ ቆይታ አደረጉ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ለይፋዊ የስራ ጉዳይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወደ ጎፋ ዞን በማቅናት በሳውላ ማዕከል የስራ ቆይታ አድርገዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ ለይፋዊ የስራው ጉዳይ ሳውላ ከተማ ስድርሱ በክልሉ የሳውላ ማዕከል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፤ በጎፋ ዞንና በሳውላ ከተማ አስተዳደር አመራሮች እንዲሁም…

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት አመራሮች በጽ/ቤቱ የ2018 ዕቅድ እና በወቅታዊ ሥራዎች ዙሪያ መከሩ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎችና አማካሪዎች በጽ/ቤቱ የ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት ዕቅድ መደበኛ ተግባራት እና በወቅታዊ ሥራዎች ዕቅድ ትግበራ ዙሪያ መክረዋል።  በምክክሩ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ ቦሻ ቦንቤ (ዶ/ር) በተጠናቀቀው የ2017 በጀት ዓመት ስራዎችን በዕቅድ በመምራት…

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በወላይታ ሶዶ ማዕከል የሚገነቡ የቢሮዎች ህንጻ ግንባታ የመስክ ምልከታ አደረጉ

ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ሶዶ ማዕከል የሚገነባ የርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ህንፃ ግንባታዎች ጅማሮ የመስክ መልከታ አድርገዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በመስክ ምልከታው ወቅት በ9 ነጥብ 5 ሄክታር መሬት ላይ የሚገነባው የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እንዲሁም…